ባላገሩ…… ባለ ሀገሩ !!!

ትውልዱ አዲስ አበባ እድገቱ ደግሞ ፍቼ ነው፡፡ ብዙዎቻችን በባላገሩ አይዶል (ምርጥ) እናውቀዋለን፡፡  ፡፡ ከ1981ዓ.ም ጀምሮ በሬዲዮ ድራማ ፀሀፊነት ፣ በተዋናይነት ፣ እንዲሁም በዘፈን ግጥም እና ዜማ ደራሲነት ለኪነጥበቡ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ አሁንም እያበረከተ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ቅዳሜ መዝናኛ የምታስታውሱትም አትጠፉም፡፡ ጠቅለል ባለመልኩ ሁለገብ ባለሙያ ነው ማለት ይቻላል፡፡

12274417_1202415089773838_817751407961024469_n

በህፃንነቱ ክራር መጫወትን የሚወደው አብርሃም ቀስበቀስ ሃርሞኒካ በመጫወት ወደ ሙዚቃው አለም እንደገባም ያወሳል፡፡ አርቲስት አብርሃም ወልዴ ባለገሩ በሚል ርዕስ ከቁጥር አንድ እሰከ ሶስት በተለያዩ ድምፃውያን አማካኝነት ስራውን ለአድናቂዎቹ አድርሷል፡፡ በሀገረ አሜሪካ ረዘም ላለ አመት ቆይታ ያደረገው አርቲስት አብርሃም ወልዴ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማ ደርሷል፡፡

12246865_1202415183107162_7834433734812452372_n

ለአብነትም ለይሁኔ በላይ – (አለምነሽ ካሳነሽ ፣ አሎልሎ) ፣ አቦነሽ አድነው – ( ባለገሩ ቁጥር 1 ሙሉ ስራ) ፣ ደሳለኝ መልኩ – ( ባላገሩ ቁጥር 2 ሙሉ ስራ ) ፣ ኤፍሬም እና ጎሳዬ – ( ባላገሩ ቁጥር 3) ፣ እጅጋየሁ ሽባባ – (ኳስ ሜዳ እና ሌሎችም) ፣ ኤፍሬም ታምሩ – (አማን ነሽ ከሚለው አልበሙ 5 ስራዎችን) ፣ ህብስት ጥሩነህ እንዲሁም ኩኩ ኩኩ ሰብስቤ ፣ ውብሸት ፍስሃ እና ማርታ አሻጋሪ በጋራ – (አያ እንግዳ እንግዳ) የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

Leave a Reply