በጋሞ 4ሺ 500 ዓመት ያስቆጠረ “ባይራ” የተሰኘ የጥንተ ሰው ቅሬተ አካል ተገኘ 

ጋሞ በተባለ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ስፍራ ሞጣ በሚባል ዋሻ እድሜው 4ሺ 500 ዓመት የሚገመት የጥንተ የሰው ቅሪተ አካል መገኘቱን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣኝ አስታወቀ። ከግኝቱ ላይ በጥንቃቄ በተወሰደ ናሙና በእፍሪካ በዕድሜ ከፍተኛ የሆነውን የዕድሜ ዘረ መል አወቃቀር ማወቅ ተችሏል። የግኝቱን ስያሜ በተመለከት የጥናት ቡድኑ የተገኘበትን የጋሞ ማህበረሰብ ቋንቋ መሰረት ባደረገ ሁኔታ “ባይራ” ብሎ የሰየመው ሲሆን ትርጉሙም የበኩር ልጅ እንደማለት ነው።
እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ በ2011 በካተሪን አርተር የሚካሄደው የዘርፈ ብዙ የጥናትና ምርምር ቡድን በጋሞ ማህበረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች መሪነት የሞጣ ዋሻን የጎበኘ ሲሆን በወቅቱም በሰበሰቧቸው መረጃዎች መሰረት ሌሎች ባለሙያዎችን በማካተት በ2012 በከፊል ባደረገው ቁፋሮ “ባይራ” የተባለውን ቅሪተ አካል ማግኘት ችሏል።”ባይራ” ከ30 እስከ 50 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ኖሮ የሞተ የአዋቂ ወንድ ቅሬተ አካል እንደሆነ በጥናቱ መረጋገጡን የቅርስ ጥናንትና ጥበቃ ባለስልጣን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply