ወይ ሰኞ ገበያ………. !!!

የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በአማራ ክልላዊ ምንግስት ከተቋቋሙት ልዩ የብሄረሰብ ዞኖች አንዱ ነው፡፡ ዞኑ በ1986ዓ.ም አጋማሽ የተቋቋመ ሲሆን በውስጡም ሁለት የከተማ መስተዳድሮች እና አምስት የገጠር ወረዳዎችን አቅፏል፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ከሚሴም ከአዲስ አበባ በደሴ መስመር በ325 ኪ፣ሜ ከባህር ዳር ደግሞ በወልዲያ መስመር 555 ኪ.ሜርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ አብዛኛው ህዝብ ኦሮሞ ሲሆን የአማራ ፣ የአርጎባ እና የአፋር ብሄረሰቦችም በዞኑ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ የዞኑ የስራ ቋንቋም ኦሮምኛ ነው፡፡

12321294_1208444982504182_588048269006915392_n

በኦሮሞ ዞን ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ገበያዎች ቢኖሩም የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ ረገድ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት የባቲ እና የሰንበቴ ገበያዎች ናቸው፡፡ከኮምቦልቻ ጅቡቲ በሚወስደው መንገድ 41 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የባቲ ከተማን እናገኛለን፡፡ ባቲ በተለያዩ የዘፈን ቅኝቶች ብዙ የተባለላት ታሪካዊ እና ዕድሜ ጠገብ ከተማ ነች፡፡ በተለይ ባቲ ከምትታወቅባቸው መካከል አንዱ ገበያዋ ሲሆን ከመርካቶ ቀጥሎ የሚገኝ ትልቅ ገበያም እንደሆነ ይነገርላታል፡፡

12308549_1208444979170849_6718003799362913020_n

ዘወትር ሰኞ ሰኞ የሚውለው የባቲ ገበያ የአርጎባ ፣ የአማራ ፣ የኦሮሞ እና የአፋር ብሄረሰቦችን ያገናኛል፡፡ ብሄረሰቦቹ ከእነ አለባበሳቸው እና አጋጌጣቸው በስፋት በገበያው ላይ መገኘታቸው ለጎብኚዎች ትልቅ እርካታን ይፈጥራል፡፡ በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራው የሰው መስቀያ ብረትም በገበያው መሀል ቆሞ ይገኛል፡፡ ይሄም የዘመኑን ታሪካዊ ገፅታ የሚያሳይ ቅርስ ነው፡፡
12289543_1208445595837454_392797551702556799_n

   ዘወትር እሁድ እሁድ የሚውለው የሰንበቴ ገበያም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን ያገናኛል፡፡ ይህም የባህል ትስስር እና ልውውጥን ከመፍጠሩም ባሻገር የጎብኚዎችን ቀልብ ይስባል፡፡

Leave a Reply