በህንድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያኖቹ ብርሀኑ ለገሰ እና ሞሲነት ገረመው 1ኛ እና 2ኛ ሆነው ጨርሰዋል

በህንድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያኖቹ ብርሀኑ ለገሰ እና ሞሲነት ገረመው 1ኛ  እና 2ኛ ሲወጡ የኤርትራው ዘረሰናይ ታደሰ 3ኛ ሆኖ ጨርሷል። የ 21 ዓመቱ ብርሀኑ ለገሰ የራሱን ስዓት በ 25 ሰከንድ አሻሽሏል። የግማሽ ማራቶን ሪከርድ የተያዘው በዘረሰናይ ታደሰ ነው። በሌላ በኩል በሴቶች ኢትዮጵያዎቹ ገነት ያለው፤ታደለች በቀለ እና ነፃነት ጉዴታ ከአራት እስከ ስድስት በተከታታይ ው ጨርሰዋል። 1ኛ ሆኖ የጨረሰው ብርሀኑ ለገሰ 27,000 USD(550000 ብር) ተሸላሚ ሆኗል።

Leave a Reply