ፊቼ-ጨምበላላ ከማይዳሰሱ የሰው ልጆች ባህላዊ ዕሴቶች አንዱ ሆኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

የሲዳማ ህዝቦች አዲስ ዓመት ክብረ-በዓል/አከባበር ናሚቢያ ላይ በተካሄደው 10ኛው የዩኔስኮ ስብሰባ 35 ከሚሆኑ የሰው ልጆች ባህላዊ አሴቶች መካካል አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ረቡዕ, ህዳር 23, 2008 ዓም መመዝገብ ችሏል፡፡ ይህም ኢትዮጲያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን ቁጥር ወደ ሁለት ከፍ አደርጎታል፡፡ እንደሚታወቀው የመስቀል በዓል አከባበር ከዚህ ቀደም ብሎ በዩኔስኮ የሰው ልጆች ባህላዊ ዕሴቶች ወካይ ዝርዝር ውስጥ አንዱ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡

ፊቼ-ጨምበላላ፣ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል በሀገር-አቀፍ ደረጃ ከማይዳሰሱ/Intangible የሰው ልጆች ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ በመለያ ቁጥር -0003 ላይ ተካቶ ተመዝግቧል፡፡ አሁን ደግሞ ኢትዮጲያ ከመስቀል በዓል በመቀጥል በዩኔስኮ(UNESCO) ወካይ ዝርዝር ውስጥ ያስመዘገበችው 2ኛው የማይዳሰስ የሰው ልጆች ባህላዊ ቅርስ በመሆን ሊመዘገብ ችሏል፡፡ የሲዳማ ብሔር በደቡብ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል በሲዳማ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ሰፍሮ ይገኛል፡፡ 14 የሚሆኑ ጎሳዎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ጎሳ ልዩ ልዩ ንዑስ ጎሳዎችና የጎሳ መሪ አለው፡፡

ምንጭ፡- unesco.org

Leave a Reply