ሊዮኔል ሜሲ ፊርማው ያረፈበት ማልያውን ለቀድሞው የባርሴሎና የቡድን ጓደኛው ሮናልዲኒሆ ላከለት

ሲቢኤስ ስፖረትስ (cbssports.com) በድረ-ገፁ ላይ ሲፅፍ፡- ከአንደኛው የባርሴሎና ክለብ ዝነኛ ተጫዋች ወደ ሌላኛው ዝነኛ ተጫዋች የተላከ በማለት ሁኔታውን ገልፆታል፡፡
ሊዮኔል ሜሲ፣ የባርሴሎና ክለብ ኮከብ አጥቂ፣ ፊርማው ያረፈበትን 10 ቁጥር ማልያውን ለቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ ተጫዋች እና ጓደኛው ለነበረው ሮናልዲኒሆ ዲ አሲስ ሞሬራ እንደላከለት ሲነገር ሰነብቷል፡፡

ሜሲ በማልያው ቁጥር ላይ ከፊርማው በተጨማሪ ልዩ የአድናቆት መልዕክቱንም ፅፎበታል፡፡ በግርድፉ ሲተረጎም እንዲህ ይላል፡-
“ለጓደኛዬ ሮኒ፣ ከእነ ሙሉ መውደዴ እና አድናቆቴ! ትልቅ የማክበር ሰላምታዬ ይድረስህ፡፡”

እንደሚታወቀው ሁለቱ ክዋክብቶች በባርሴሎና ክለብ እ.ኤ.አ ከ2004 – 2008 አብረው መጫዎታቸው እና ዋንጫዎችንም ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

ሮናልዲኒሆ በእንስታግራም አካውንቱ ላይ የሜሲ ፌርማ ያረፈበትን ማልያ ፎቶ አንስቶ እንዳስቀመጠው
ሮናልዲኒሆ በኢንስታግራም አካውንቱ ላይ የሜሲ ፌርማ ያረፈበትን ማልያ ፎቶ አንስቶ እንዳስቀመጠው

ሮናልዲኒሆ የሜሲ ስጦታ እንደደረሰው በኢንስታግራም ገፁ ላይ ስላበረከተለት ስጦታ እንዲሁም ስላስታወሰው በይፋ ከልብ አመስግኗል፡፡ የሜሲ ፌርማ እና የአድናቆት መልዕክት ያረፈበትን ማልያ ፎቶ በማንሳት በኢንስታግራም/instagram አካውንቱ ላይ አስቀምጧል፡፡ ከፎቶው ስርም የምስጋና መልዕክቱን አስፍሯል፡፡ 172.8k (172,800) የሚሆኑ ውደሳዎች – likes እና 935 አስተያየቶች – comments በዚህ ፎቶ ግርጌ እንደተፃፈበት ያሳያል፡፡

Leave a Reply