ኢትዬጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በአሰሪዋ ልጅ ላይ በመጥረቢያ ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢትዬጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የቀጣሪዎቿን ሴት ልጅ አሰሪዎቿ እስኪወጡ ጠብቃ በመጥረቢያ ጉዳት እንዳደረሰችባት ያገኘነው የዜና ምንጭ ያስረዳል፡፡

ተጎጅዋ በጥቃቱ ምክንያት ፊቷ፣አንገቷ፣ሆዷ አካባቢ እና የተለያዩ መገጣጠሚያዎቿ ላይ ጉዳት ደርሶባታል፡፡ወደ ሆስፒታል ከተወሰደች በኃላ የህክምና ባለሙያዎች ነፍሷን ለማትረፍ እንደተረባረቡ ተጠቅሷል፡

ልጅቷ ጉዳቱ በተፈፀመበት ወቀት በአንገት ስብራት ምክንያት ለሰባት አመታት የአልጋ ቁራኛ ሆና በቤት ውስጥ የምትኖር ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳት ገና በፖሊስ እየተጣራ መሆኑ ታውቋል፡፡

ተጎጂዋ በአሁኑ ሰዓት በማገገም ላይ እንዳለች የህክምና ባለሙያዎቹ ገልፀዋል፡፡ የዜና ምንጩ ስለ ተጎጂዋ እድሜ የጠቀሰው መረጃ የለም፡፡

ምንጭ፡-emirates247.com

Leave a Reply