ኦባማ ማክሰኞ ቃለመሀላ በመፈፀም ወደ አሜሪካ ዜግነታቸውን የሚቀይሩትን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ26 ሀገሮች የተወጣጡት 31 ሰዎች በተገኙበት ንግግር ሊያደርግ ነው

ኦባማ ንግግሩ የሚያደርገው በዋናው ሙዜየም(National Archives Museum) በመገኘት ሲሆን ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በተፈጠረው የሽብርተኞች ጥቃት ላይ መሠረት ያደረገ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል

ንግግሩ የሚያተኩረው

  1. የአሜሪካን ሕዝብ በራስ መተማመን ለመመለስ
  2. ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ስደተኞች በአሜሪካ ውስጥ ሲኖሩ የሚጠበቅባቸውን አላፊነቶችን እና ግዴታዎችን ለመጠቆም
  3. ሪፖብሊካንን ወክሎ ለአሜሪካ መሪነት እየተወዳደረ የሚገኘው ዶናል ትራምፕ ሙስሊሞችን እና ስደተኞችን አስመልክቶ ጠንከር ያለ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ አሜሪካ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር እየሻከረ የመጣውን ግንኙነት ለመቀልበስ ነው።

 

Leave a Reply