የቻምፒዮንስ ሊግ ምርጥ 16 ቡድኖች የጥሎ ማለፍ ውድድር ድልድል ይፋ ሆነ

ዛሬ ሰኞ፣ ታህሳስ 4፣ 2008 ዓም በኒዮን ስዊዘርላንድ የ2015/16 አውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ 16 ምርጥ ክለቦችን እርስ በእርስ የሚያገናኛቸው የዕጣ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በድልድሉ መሰረት 8 ምርጥ ክለቦችን ለመለየት በሚድረገው የመጀመሪያው ዙር ጥሎ ማለፍ ውድድር የሚከተሉት ክለቦች በደርሶ መልስ የሚጫወቱ ይሆናል፡-

1. Gent(ከቤልጅየም) vs Wolfsburg (ከጀርመን)
2. Roma(ከጣሊያን) vs Real Madrid(ከስፔን)
3. Paris St-Germain(ከፈረንሳይ) vs Chelsea(ከእንግሊዝ)
4. Arsenal(ከእንግሊዝ) vs Barcelona(ከስፔን)
5. Juventus(ከጣሊያን) vs Bayern Munich(ከጀርመን)
6. PSV Eindhoven(ከሆላንድ) vs Atletico Madrid(ከስፔን)
7. Benfica (ከፖርቹጋል) vs Zenit St Petersburg(ከራሽያ)
8. Dynamo Kiev(ከዩክሬን) vs Manchester City(ከእንግሊዝ)

በዝርዝሩ መሠረት በመጀመሪያ የተጠቀሱት ስምንት ክለቦች የመጀመሪያውን ጥሎ ማለፍ ውድድር ተጋጣሚያቸውን ክለብ በሜዳቸው የሚያስተናግዱት ናቸው ማለት ነው፡፡

በዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ምርጥ 16 ክለቦች ዕጣ ድልድል ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ እንግሊዝ እና እስፔን እያንዳንዳቸው በ 3 ክለቦች ይወከላሉ፡፡ ጀርመን እና ጣሊያን ደግሞ እያንዳንዳቸው በ 2 ክለቦች የተወከሉ ሲሆን፣ የተቀሩት ቤልጅየም፣ ፈረንሳይ፣ ራሽያ፣ ዩክሬን፣ ፖርቱጋል እና ሆላንድ ደግም እያንዳንዳቸው በ 1 ክለብ ይወከላሉ ማለት ነው፡፡

እንደሚታወቀው 16ቱ ምርጥ ክለቦችን ለጥሎ ማለፍ ውድድር የሚያገናኘው የዕጣ ድልድል ከአንድ አገር የሚወከሉ ክለቦችን እርስ በእርስ አያገናኝም፡፡ ለምሳሌ፣ እንግሊዝን የወከሉት አርሴናል፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ በዚህኛው ዕጣ ድልድል እርስ በእርስ እንዲገናኙ አይደረግም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከምርጥ 16 ክለቦች፣ የመጨረሻዎቹ ምርጥ 8 ክለቦች ከታወቁ በኋላ የሚደረገው የዕጣ ድልድል ከአንድ አገር የሚወከሉ ክለቦችን እርስ በእርስ የሚያገናኝ ይሆናል፡፡

የዘንድሮው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ውድድር በጣሊያኗ ሚላን ከተማ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

Leave a Reply