ኢትዮጵያ የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ጉባኤን ልታስተናግድ ነው

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን የሚመለከተው ኮሚቴ ጉባኤን በቀጣዩ አመት አዘጋጅ ሀገር ሆና ተመረጠች፡፡ አስራ አንደኛው ጉባኤ ከህዳር 19 ጀምሮ ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል፡፡
ጉባኤውን ማዘጋጀቷ የኦሮሞ ገዳ ስርዓትን በአለም የሰው ልጅ ወካይ ባህላዊ ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር መሆኑን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል፡፡ዩኔስኮ በአስረኛ ጉባኤው ፍቼ ጨምበለላን በማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር የዓለም ቅርስ አድርጎ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ኢብኮ

Leave a Reply