ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ባለፉት 3 ወራት ውስጥ ብቻ ከ880 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ባለፉት 3 ወራት ውስጥ ብቻ ከ880 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማድረጓን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ሃገሪቷን የሚጎበኙ የውጭ ቱሪስቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቆሙት አቶ ገዛህኝ አባተ ባለፉት 3 ወራት ውስጥ 235,000 በላይ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንደጎበኙ ተናግረዋል ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። በሚኒስቴሩ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛህኝ አባተ እንደተናገሩት ከሆነ የቱሪስት ፍሰቱና ገቢው ሊጨምር የቻለው የአገሪቱን ባህላዊ ፤ተፈጥሮዋዊና ታሪካዊ ቅርሶችን የማስተዋወቅ ሥራዎች በመሰራታቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ከ734,000 ቱሪስቶች በላይ  ሀገራችን የገቡ ሲሆን በዚህ ዓመት ቁጥሩ ወደ 1ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ይጠበቃል ገቢው ደግሞ ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንደሚል ያጠበቃል።

Leave a Reply