ጤፍ ለኢትዮጲያ፣ ኢትዮጲያ ለጤፍ፣ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች

በእኔ ዕምነት እና አስተሳሰብ ጤፍ ከኢትዮጲያዊያን መገለጫዎቻችን አንዱ የሆነ፣ የአመጋገብ ስርዓታችን ላይ መሰረት የጣለ፣ ሀብታችን እና መለያችን ነው፡፡ ይህን ሀሳብ እና ስሜት ብዙ ኢትዮጲያዊ እህት-ወንድሞቼ  ይጋሩታል የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

ወደ ዋናው ሀሳቤ ስመለስ፡-
እንደፈረንጆቹ ቀን አቆጣጠር በ2005 በኢትዮጲያ እና በአንድ የሆላንድ/ኔዘርላንድ ድርጅት(HPFI) መካከል በተደረገ ስምምነት መሠረት፤ 12 ዓይነት የኢትዮጲያ የጤፍ ዝርያዎች ላይ ምርምር እንዲያደርግ  ተፍቅዶለት ነበር፡፡ የምርምር ይሁንታ ስምምነቱ ለHPFI ለተባለው ድርጅት ጤፍ-መሰል አዲስ ምርት እንዲያበለፅግ እና ምርቱንም ለአውሮፓዊያን ገብያ ማቅረብ እንዲችል የሚፈቅድ ነብር፡፡ በዚህም ድርጅቱ ከሚያገኘው ጥቅም ቀላል የማይባለውን ድርሻ ለኢትዮጲያ እንዲያጋራ/እንዲሰጥ የሚያደርግ ስምምነት ተደርጎ ነበር ፡፡

ዳሩ ግን ከምርምሩ ውጤት ሲጠበቅ የነበረው መልካም አጋጣሚ ግቡን ሳይመታ የውሃ ሽታ ሆነ ቀርቷል፡፡ እስካሁን ኢትዮጲያ ያገኘችው ነገር ቢኖር 4000 ዩሮ እና በጊዜ የተቋረጠው እና አናሳው የምርምር ፕሮጀክት ነው፡፡ ከዚያም፣ እንደፈረንጆቹ ቀን አቆጣጠር በ2009፣ ከላይ ስሙን የጠቀስኩት ድርጅት ከሰርኩ በሚል ሰበብ ስራውን አቆመ፡፡ ስራውን ከማቆሙ በፊት ቀደም ባሉት ዓመታት ግን ድርጅቱ ከአውሮፓ የፓተንት ቢሮ ጤፍን በተለያየ መልኩ (በዱቄት፣ በቡኬት መልክ እና ሌሎች ጤፍ-መሰል ምርቶችን) አቀነባብሮ የመሸጥ መብት አግኝቶ ነበር፡፡ በመቀጠል ይህ ድርጅት ከመዘጋቱ በፊት ያገኘውን የፓተንት መብት ሙሉ በሙሉ ለሌላ አዲስ ለተቋቋመ ድርጅት ሸጠ፡፡ ልብ ይበሉ! የአዲሱ ድርጅት ባለቤቶች ደግሞ <<ከሰርኩ ባዮ ድርጅት>> መስራቾች የነበሩ መሆናቸው ነገሩን ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የማጭበርበር ሴራ እንደሆነ ያሳየናል፡፡

ጤፍ እና ከጤፍ ጋር ተያይዞ የሚመረቱ ምርቶች፣ ምግቦች እና መሰል ነገሮች በኢትዮጲያ ገበሬዎችና መላ ህዝቧ ለሺዎች አመታት ተይዞና ተጠብቆ የኖረ፤ የእኛው ሀብት መሆኑ እና መብቱ ያላት ኢትዮጲያ ብቻ እንደሆነች ለሚመለከው ሁሉ ልናሳውቅ ይገባል፡፡

በዚህ ሠዓት ከእኛ ምን ይጠበቃል? ምንስ ማድረግ እንችላለን . . . ?
የሚከተውን ሊንክ በመጠቀም፣ የአውሮፓ ፓተንት ቢሮ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ቤኖይት ባቲስቴሊ“የሆላንዱ/ኔዘርላንዱ ድርጅት በማጭበርበር የወሰደው የጤፍ ማቀነባበር የፓተንት መብት እንዲሰረዝ” የሚጠይቀውን ፊርማ/ፔቲሽን በመፈረም የድርሻችሁን እንድትወጡ የከበረ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ እባክዎን የሚከተለውን ሊንክ ክሊክ ያድርጉ፡-

የጤፍ ምርት/ምርቶች መብት የሚገባት ኢትዮጲያ እንጂ ሌላ ማንም እንዳልሆነ ለማሳወቅና ለመጠየቅ የተደረገ ጥሪ/ፒቲሽን

ሊንኩን ተጠቅማችሁ ስትገቡ ከድረ-ገፁ በስተቀኝ  SIGN THE PETITION ከሚለው ስር የኢ-ሜይል አድራሻችሁንስማችሁንአገራችሁን፣ ያላችሁበትን ከተማ እና ካስፈለገም ምክንያታችሁን በመግለጽ ፔቲሽኑን መፈረም ትችላላችሁ፡፡

Leave a Reply