የጢስ ዓባይ ፏፏቴ…..

ከባህርዳር ከተማ በስተምስራቅ በ30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከጢስ ዓባይ ከተማ አጠገብ የሚገኘው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ በ400 ሜትር ስፋት ከ40 እስከ 50 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል የሚወረወር ሲሆን እጅግ አስገራሚና አስደሳች ከሆኑት የተፈጥሮ ክስተቶች አንዱ ነው፡፡ እየተጥመለመለ ወደ ገደሉ ከሚወርደው ውሃ የሚፈጠሩት ብናኝ የውሃ ፋንጣሪዎችም አካባቢውን በጢስ የተሸፈነ ያስመስሉታል፡፡ የፏፏቴው ነጐድጓዳማ ድምፅና የአካባቢው ልምላሜ፣ በፏፏቴው ከሚፈጠረው ቀስተ ደመና ጋር ተዳምሮ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል፡፡
10308130_1230760660272614_7765684006371128292_n

ከጢስ ዓባይ ከተማ ፏፏቴው ለመድረስ ሁለት አማራጮችን መጠቀም ይቻላል፡፡የመጀመሪያው አማራጭ ከጢስ ዓባይ ከተማ 1.5 ኪ.ሜ በመኪና በመጓዝ ለመኪና ማቆሚያ ከተዘጋጀው ቅጥር ግቢ ከደረሱ በኃላ ለ20 ደቂቃ የእግር መንገድ ተጉዘው ፏፏቴውን ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ወንዙን በሞተር ጀልባዎች በማቋረጥ ወደ ፏፏቴው የሚወስደው መንገድ ነው፡፡ ይኸኛውን አማራጭ ለመጠቀም ከከተማው ሰሜናዊ ምዕራብ የሚገኘውን የገበያ ስፍራ አቋርጦ ከወንዙ መድረስን ይጠይቃል፡፡ በዚህ መንገድ ወደ ፏፏቴው ለመዝለቅ ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ይወስዳል፡፡ ወደ ፏፏቴው በሚወስደው የእግር መንገድ አካባቢ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአፄ ሱሰንዮስ ዘመነ መንግስት እንደተሰራ የሚነገርለት የአላታ ድልድይ ይገኛል፡፡ ይህ በአባይ ወንዝ ላይ የተሰራ የመጀመሪያው ድልድይ እንደሆነም ይነገራል፡፡

Leave a Reply