ኒውስዊክ የዛሬ 40 አመት ገደማ ተከታዩን ደብዳቤ ለደርግ ፅ/ቤት ፅፎ ነበር …….

ኒውስዊክ የዛሬ 40 አመት ገደማ ተከታዩን ደብዳቤ ለደርግ ፅ/ቤት ፅፎ ነበር ……. / ደብዳቤው ይህን ይላል/
Tafesse-Ethiopian-Tourism

 

“ይህ ደብዳቤ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ቱሪስት ድርጅት ሃላፊ አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ ምህረት ይደረግላቸው ዘንድ ለደርግ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የተላከ ነው ፡፡ በፍርድ ቤቱ ችሎት ጣልቃ የመግባት ፍላጎት የለኝም፡፡ ይሁንና ሀብተስላሴ ታፈሰ በምርመራ ወንጀለኛ ሆነው እንኳን ቢገኙ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ለሀገራቸው ያደረጉትን አስተዋፅኦ ከግምት እንዲያስገባ እማፀናለሁ፡፡ የኒውስዊክ የአፍሪካ ቢሮ ሃላፊ እንደመሆኔ ሀብተስላሴ ታፈሰ የቱሪዝም ሚኒስትር ብቻ ናቸው አልልም፡፡ መንግስት ያልሾማቸው የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው፡፡ ያልገባሁበት የአፍሪካ ሀገር የለም ሀብቴን የሚወዳደር አፍሪካዊ ሚኒስትር ግን አላየሁም፡፡ ሀብተስላሴ ሁሉ ነገር ቢሟላላቸው ኢትዮጵያን በቱሪዝም የአፍሪካ ቁንጮ እንደሚያደርጓት አልጠራጠርም፡፡ ቱሪዝም ያለ እሳቸው ትርጉም የለውም፡፡ ልማትን የምትሻ ኢትዮጵያ እኚህን ታላቅ ሰው ብታጣ እጅግ አሳፋሪ ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቱም ለምን ይህን ያህል እንደምወተውት ሳይረዳ ይቀራል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ”

አቶ ሃብተሥላሴ ታፈሰ (የቱሪዝም አባት) በቅርስና ባህል – የ2007 ዓ.ም. በጎ ሰው ተሸላሚም ሆነዋል፡፡

Leave a Reply