የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ

በ1962 ዓ.ም የተመሰረተው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከአ.አ. በ4ዐዐ ኪ.ሜ ርቀት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡ ስፋቱ ወደ 22ዐዐk.m2 የሚደርስ ሲሆን ከሰሜን ወደ ደቡብ 74 ኪ.ሜ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ደግሞ 53 ኪ.ሜትር ይሰፋል፡፡ ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከ145ዐ እስከ 4377 ጫማ ባለ ልዩነት ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎችን ያካትታል፡፡ 4377 ጫማ የሚረዝመው እና ከኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የቱሊ ዲምቱ ተራራን ጨምሮ የአፍሮ አልፓይን ከፍተኛ ቦታዎች በዚህ ፓርክ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የባሌ ተራሮች ከፍተኛ አካባቢ በተለያዩ መንገድ የተፈጠሩ ሀይቆች፤ እርጥበት አዘል መሬቶች፣ የእሳተጎሞራ ቅሪቶችን አቅፎ ይዟል፡፡

10349157_10203515824870250_7315874229482932133_n

ፓርኩን ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር በኢትዮጵያ ትልቁና ወደ ሰባት ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሚሸፍነው ‹‹የሐረና ደን›› በውስጡ በመገኘቱ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንድ ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሆነው በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ሲገኝ የተቀረው ስድስት ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር ድርሻ በኦሮሚያ ክልል የደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ ይተዳደራል፡፡ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ጊዜያዊ መዝገብ ውስጥ ተካቷል፡፡

10671352_10203515821190158_867122574676965949_n     ከዚህም ሌላ ከ1600 በላይ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ዓይነት ዕፅዋቶች፣ 78 ዓይነት አጥቢ የዱር እንስሳትና ወደ 200 የሚጠጉ አእዋፋት በፓርኩ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል 32 ዓይነት ዕፅዋቶች፣ 31 የሚጠጉ ብርቅዬና ድንቅዬ የዱር እንስሳትና ወደ ስድስት የሚጠጉ ዕፅዋት በብሔራዊ ፓርኩ ካልሆነ በስተቀር በሌላው ዓለም ፈጽሞ አይገኙም፡፡ በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 78 የሚደርሱ አትቢ የዱር እንሰሳት 17 የሚሆኑት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ እንሰሳት ናቸው፡፡

   ከዚህ ባሻገር ለሳይንስና ኢኮሎጂ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው በደረታቸው የሚሳቡ ልዩ ልዩ እንስሳትና መንቆረርቶችን ፓርኩ አቅፎ ይዟል፡፡ ቡናና በኢትዮጵያ ውስጥ ለባህል መድኃኒትነት የሚውሉ 40 ከመቶ ዕፅዋቶችም ይገኙበታል፡፡ በእፅዋት እና በእንሰሳት ብዝሃ ህይወት መበልፀግ ደረጃ ፓርኩ ከአለም 34ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የባሌ ብሄራዊ ፓርክ በ “Bird lite International” በአለም ከሚገኙ አስፈላጊ የአዕዋፍ መኖሪያ ቦታዎች ጎራ ተመድቧል፡፡

በፓርኩ ከ28ዐ በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች ሲኖሩ ሲሆን ሰባቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡እንደ ዓለም አቀፍ የወፎች ድርጅት ሪፖርት ከሆነ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የአፍሪካ አራተኛው ‹‹በርዲንግ ሳይት›› ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ በባሌ ብሄራዊ ፓርክ ዋቢ ሸበሌ፣ ዌብ፣ ዱማል፣ ያዶት እና ወልመል የተሰኙ ወንዞች ይፈሳሉ፡፡ በባሌ ብሄራዊ ፓርክ ከሚገኙ የዱር እንስሳት መካከል ቀይ ቀበሮ፣ኒያላ ፣ አጋዘን እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ

95647017_14-660x431

ይህ ቀይ ቀበሮ አኗኗሩ በመንጋ ነው፡፡ አንድ መንጋ ከ3-13 አባላት ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ እያንዳንዱ መንጋ የራሱ የመኖሪያ አካባቢ ሲኖረው የአካባቢውን ድንበር ወንድ ቀይ ቀበሮዎች ያስከብራሉ፡፡ በርቢ ወቅት ሴት ቀይ ቀበሮ ከመንጋው አባላት ወንዶች ውጪ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድለትም፡፡ ከመንጋው አባላትም ጠንካራው ወንድ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ የተሻለ እድል አለው፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ ከማህበራዊ አኗኗራቸው ባሻገር በጠንካራ አዳኝነታቸው ጭምር ይታወቃሉ፡፡

ኒያላ /Mountain Nyalas/

10703629_10203515822990203_8616326608578496337_n

ይህ የአጋዘን ዝርያ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ እንስሳ ነው፡፡ ቁመቱ 135 ሴ.ሜ በአማካኝ ይደርሳል፡፡ ሴቷ ኒያላ ከ15ዐ — 2ዐዐ ኪ.ግ ወንዱ ደግሞ ከ18ዐ–3ዐዐ ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ ኒያላ በባሌ ተራራማ አካባቢዎች ቁጥቋጦ፣ ሳር እና ዘርዘር ያለ የደን ሁኔታ በሚታይበት አካባቢ በስፋት ይኖራል፡፡ አንዲት ሴት ኒያላ ከ8-9 ወራት የሚቆይ የእርግዝና ጊዜ የሚኖራት ሲሆን በአንድ ጊዜ አንድ ትወልዳለች፡፡ ግልገል ኒያላ በመኖሪያ አካባቢው ብቻውን መንቀሳቀስ ከመጀመሩ በፊት ለ2 አመታት ያህል ከእናቱ አይነጠልም፡፡ ከዚህ በኋላ ሴቶች ወዲያውኑ የሚያረግዙ ሲሆን ወንዶቹ ወደ ላጤዎች ምድር ይቀላቀላሉ፡፡ ኒያላ ሳር፣ቅጠላ ቅጠል እና ቁጥቋጦ ይመገባል፡፡

Harenna forest, Bale Mountains National Park, Ethiopia

የባሌ ብሄራዊ ፓርክ አስደናቂ የተራራ እይታዎች፣ ልዩ ስሜት የሚፈጥሩ ደኖች እና የውሃ አካላት ለቱሪስቶች ልዩ መስህብ ናቸው፡፡ በፓርኩ የሚገኙ የዱር እንስሳት እና አዕዋፍ ስብጥርም አስደናቂ ነው፡፡ ወደ ፓርኩ የሚጓዙ ቱሪስቶች የፓርኩን ተራራዎች በእግር በመውጣት /Trekking/ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡ በፓርኩ የሚገኙ የዳንካ፣ ዌብ እና ሻንያ ወንዞች እና ልዩ ልዩ የውሀ አካላት አሳ በማጥመድ ለሚዝናኑ ሀገር ጎብኝዎች የተለየ የእርካታ ምንጭ ናቸው፡፡ አሳ ለማጥመድ ግን ከፓርኩ አስተዳደር ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

Leave a Reply