የአደዋ አርበኛዋ እቴጌ ጣይቱ

እቴጌ ጣይቱ ከሕዝቡ ጋር በነበራቸው ግንኙነት በተለይም ያሳዩት በነበረው ርህራሄና ልግስና በጣም የተወደዱና የተመሰገኑ በመሆናቸው በሚያውቋቸው ዘንድ በሰፊው ይወራላቸዋል። ግልፅ የሆነው የፖለቲካ አስተያየታቸውና ጽኑ የሆነው ተግባራዊ ውሳኔያቸው፣ ዘዴንና ሥልጣንን እንዲሁም ምክርን፣ ኃይልን ምን ጊዜ፣ በእንዴት ያለ መጠን መጠቀም እንዳለባቸው በትክክል የመገመት ችሎታቸው ሲታይ በዓለም ከታወቁት የፖለቲካ አርበኞች ውስጥ ሊወሳ የሚገባ ታሪካዊ ስፍራ እንዳላቸው አጠራጣሪ አይሆንም።

10314499_10204667619144387_8244187981750086452_n

ስመ ጥሩነታቸውን ለማትረፍ ካስቻሏቸው ጉዳዮች ጽኑ በሆነ መንፈሳዊ ኑሮአቸው አኳያ የሚታየው የልግስናና የቤተ ክርስቲያን ነፃ ተግባሮች አንዱና ዓይነተኛው ነው። ይህ ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ልዩ ግንኙነት ለመመስረት ያስቻላቸው ከመሆኑም በላይ የፖለቲካ ሥልጣናቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ከሌሎች ታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች ታሪካዊ አነሳስ ለመገንዘብ ይቻላል።

Leave a Reply