በኢትዮጵያ ሬዲዮ የመጀመሪያዋ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ እና ኢትዮጵያዊት ነርስ…….

ልዕልት ፀሀይ ፀሀይ ኃይለስላሴ እ.ኤ.አ በ1919 ተወልዳ በ1942 በወሊድ ምክንያት በ23 አመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች፡፡ ልዕልት ፀሐይ በእንግሊዝ አገር በቆየችበት አምስት የስደት አመታት የነርስነት ሙያን አጥንታለች፡፡ ወደ ሀገሯ ከተመለሰች በኋላም በአገሪቱ ውስጥ በጊዜው በተለያዩ ቦታወች በነበሩት የሕክምና ተቋማት በመዘዋወር በበጎ – ፈቃደኝነት አገልግላለች፡፡ እንዲሁም የተለያዩ የአውሮጳ ቋንቋወች ችሎታ ስለነበራት በቤተ መንግስት ደረጃ አስተርጉዋሚ በመሆን ለተወሰነ ጊዜ እንዳገለገለች ድርሳናት ያወሳሉ፡፡

4622560450_5230929bfe

ልዕልት ፀሀይ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የመጀመሪያዋ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ እና የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ነርስ እንደነበረች ይነገርላታል፡፡ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀምሌ 14 ቀን 1923 ዓ.ም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በነፋስ ስልክ ለሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ፡፡ይህ ጣቢያ የተቋቋመው አንሰልዶ በተባለ የጣሊያን ኩባንያ ነበር፡፡ የንፋስ ስልክ የሬዲዮ ጣቢያ ተመርቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ስርጭት የጀመረው መስከረም 2 ቀን 1928 ዓ.ም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
10413394_996808553667827_6606237474507800646_n  ከንጉሱ ንግግር በማስከተልም ልጃቸው ልዕልት ፀሀይ በእንግሊዘኛ ንግግር አሰምተዋል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የሬዲዮ ስርጭት ታሪክ የመጀመሪያው የእንግሊዘኛ ቋንቋ መልዕክት መሆኑ ነው ፡፡ የልዕልት ፀሀይ አስከሬንም በታዕካ ነገስት በዓታ ለማሪያም ገዳም ሙዚየም ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ በሙዚየሙ ውስጥ የንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ፣ የንግሰተ ነገስት ዘውዲቱ ምኒልክ ፣ የልዕልት ፀሀይ ኃይለስላሴ እና የግብፁ ጳጳስ የአቡነ ማቴዎስን መካነ መቃብር እና ሌሎች በርካታ ቅርሶችን ይመለከታሉ ፡፡ ጎራ ይበሉ በሚያዩት ነገር ደስተኛ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

Leave a Reply