ወታደራዊ የስለላ ጥበብ ለአድዋ ድል …….

ጦርነት ከመካሄዱ አስቀድሞ የጠላትን ጦር አቋም እና አሰላለፍ መሰለል ያለ ነው፡፡ የአድዋ ጦርነት ከመካሄዱ በፊትም ኢትዮጵያም ጣሊያንም አንዳቸው በሌላኛው ላይ ይሰልሉ ነበር፡፡ በወቅቱ የጣሊያን መንግስት መረጃ አቅራቢ(ሰላይ) የነበሩት ባሻ አውዓሎም ለኢትዮጵያም መስራት ጀመሩ፡፡ የጦርነቱ ጊዜ ሲቃነብም አውዓሎም ከአጤ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ጋር መከሩ፤ አንድ ዘዴ /መላም/ ቀየሱ፡፡ የካቲት 23 ቀን መኳንንቱ ሰንበትንም ፣ የጊዮርጊስንም ዕለት ለማክበር ወደ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳሉ፡፡ ሰራዊቱም ቀለብ ለመፈለግ በየመንደሩ ይበተናል፤ በዚህ ጊዜ ምኒልክ እና ጣይቱን በቀላሉ እንደሚማርኩ በማረጋገጥ አውዓሎም ጄኔራል ባራቴሪን እንዲያሳምን ተደረገ፡፡ ባራቴሪም የአውዓሎምን መረጃ በመቀበል ወዲያው ለሰራዊቱ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ጦሩም የካቲት 22 ከምሽግ ወጣ የጣሊያን ጦር ማለዳ መንቀሳቀሱንም ለአጤ ምኒልክ በመልዕክተኛ ተነገራቸው፡፡ ከዚያም ጦርነቱ ይጀመራል ፡፡
12794487_1269331219748891_927581741855353711_n

ባሻ አውዓሎም የጣሊያንን ጦር እየመሩ ከፊት ከፊት ይሄዱና የኢትዮጵያ ጦር የመሸገበት ሲደርሱ እሳቸው ዘለው ከኢትዮጵያ ጀግኖች  ጋራ በማበር ጣሊያንን በመፋለም ለአደዋ ድል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ ለፈፀሙት አገልግሎት  እና ጀግንነትም የእንጥጮ ወረዳ አስተዳዳሪ ሆነው ተሾመውም ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ባሻ አውዓሎም ሀረጎት በ1844ዓ.ም በትግራይ ክልል  አደዋ እንጥጮ ወረዳ እንደተወለዱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የራስ አርአያ ድንቅ ወታደርም ነበሩ፡፡ በልጅነታቸው ራስ አርአያ በመተማ ጦርነት ሲሞቱ አውዓሎም የራስ መንገሻ አሽከር ሆኑ፡፡ የባሻነት ማዕረግ የሰጧቸውም ራስ መንገሻ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ባሻ አውዓሎም በተወለዱ በ78 ዓመታቸው ህዳር 12፣ በ1922ዓ.ም ባደረባቸው ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ክብር ለአድዋ ጀግኖች እና ሰማዕታት !!!

Leave a Reply