የፊልም ደራሲ፣ አዘጋጅ እና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የካቲት 25 ቀን 1938 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ከደራሲ አባታቸው ገሪማ ታፈረናከመምህርት እናታቸው ተወለዱ፡፡ በአሁኑ ወቅት ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ  የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም 70 ዓመታቸውን ያከብራሉ፡፡ ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ በአባታቸው በአቶ ገሪማ የትያትር ቡድን ውስጥ በመስራት ነበር፤ ወደ ኪነ ጥበቡ የገቡት፡፡ ብዙውን ጊዜም ታሪካዊ እና እውነተኛ የኢትዮጵያን ባህል የሚያንፀባርቁ ወጥ ድራማዎችን ይሰሩ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ያደጉት ሀይሌ በ21 ዓመታቸው ነበር ወደ ውጭ የወጡት፡፡

እ.ኤ.አ በ1967 ወደ ቺካጎ ጉድማን የድራማ ት/ቤት ለመማር ከሄዱ በኋላ ሲኒማ ከትያትር የበለጠ ማሳየት የፈለገውን ሁሉ ማሳየት ስለሚያስችለኝ በማለት ወደ ፊልሙ አዘነበሉ፡፡በዚህም መሰረት ከካሊፎርኒያ ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን “Bachelor’s and Master’s of Fine Arts degrees in film” አግኝተዋል፡፡ ፕሮፌሰር ሀይሌ ከመምህርነታቸው ጎን ለጎን የሚሰሯቸው የፊልም ስራዎች በይዘት እና አቀራረባቸው ከሌሎች ፊልሞች ይለያሉ፡፡  “ ጤዛ”  የተሰኘውን  ፊልም  በአማርኛ  በመስራት  ብቃታቸውን  በኢትዮጵያውያን  የፊልም  ታዳሚዎች  ዘንድ ያስመሰከሩት  ፕሮፌሰሩ  በአለም  ዓቀፍ  ደረጃም  እውቅና  ያገኙባቸውን  በርካታ  ፊልሞች  ሰርተዋል፡፡ በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ  በኢትዮጵያ  የነበረውን  ፖለቲካዊ፣  ማህበራዊና  ባህላዊ  ሁኔታ  ማራኪ  በሆነ  አቀራረብ ባሳዩበት  “ጤዛ  ፊልም”  በጎንደርና  በአዲስ አበባ  ከተሞች  እንዲሁም  በጀርመን  ሀገር  የኢትዮጵያውያንን  አኗኗር ፍንትው  አድርገው  አሳይተዋል፡፡

ፕሮፌሰር  ኃይሌ  ገሪማ  በ“ጤዛ ፊልም”  በአማርኛ  ፊልሞች  ላይ  ተሞክረው  የማያውቁ  የፊልም  አሰራር ቴክኒኮችን  በመጠቀም  እና  ፊልም  እንኳን  ተውነው  ተመልክተው  የማያውቁ  ተዋናዮችን  በማሳተፍ  አስደናቂ የፊልም  ዳይሬክቲንግ  ብቃታቸውን  አሳይተዋል።  በጎርሳውያኑ  አቆጣጠር  ከ1975  ጀምሮ  በሀዋርድ  ዩኒቨርስቲ የፊልም  አሰራር  ጥበብ  መምህር  ሲሆኑ  በጎርሳውያኑ  1993  በሰሩት  “ሳንኮፋ ፊልም”  ከፍተኛ  አለምአቀፍ እውቅና እና ተቀባይነትን  አግኝተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ከሰሯቸው ፊልሞች ሰባት ያህሉ በተለያዩ የአለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተሸላሚ ናቸው፡፡ ፊልሞቻቸው በአፍሪካውያን እና በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው፡፡ የራሳቸውን እንዲሁም ስለ አፍሪካውያን እና በአፍሪካውያን የተሰሩ ፊልሞችን የሚያሰራጩበት “ማይ ፈዱ” የተባለ ፊልም ማሰራጫ  ድርጅትም አላቸው፡፡

Gerima, left, receives an award from Emperor Haile Selassie of Ethiopia

ፕሮፌሰር  ሀይሌ  ገሪማ  ከሰሯቸው  ፊልሞች  መካከልም ፡-
1972 – Hour Glass Hour Glass

1972 – Child of Resistance

https://www.cinema.ucla.edu/la-rebellion/films/child-resistance
1976 – Bush Mama

1976 – Mirt Sost Shi Amit (also known as Harvest: 3,000 Years)

1978 – Wilmington 10 — U.S.A. 10,000
1982 – Ashes and Embers
1985 – After Winter: Sterling Brown
1993 – Sankofa

1994 – Imperfect Journey

1999 – Adwa – An African Victory
2009 – Teza


የካቲት 25 የፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ልደት ነውና መልካም ልደት !!! ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኝቻለሁ፡፡

Leave a Reply