የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ

  • NALE LOGO1 ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት “የሕህብ ቤተመጻሕፍት ወመዘክር” በሚል ስያሜ በ1936 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረውም ንጉሱ ባበረከቱት ከ 200 በላይ የመጻሕፍት ስጦታ ነው፡፡
  • በ1958 ዓ.ም በተደረገው የቤተመጻሕፍት መዋቅር ለውጥ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የሚል ስያሜ ይዞ በጥንታዊ ቅርሶች አስተዳደር ሥር እንዲሠራ ተደረገ፣ በ1967 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ ተዋቅሮ ሥራውን ቀጠለ፡፡
  • በ1968 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 50/68 ለባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚ/ር በሀገር ውስጥ ከሚታተሙ ማናቸውም ህትመቶች ሶስት ሶስት ቅጂዎችን እንዲረከብ በመንግስት የተሰጠውን ሥልጣን ቤተ-መጻሕፍቱ እንድያስፈጽም ውክልና አገኘ፡፡
  • በ1972 ዓ.ም ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት መምሪያ ተብሎ ስራውን እንድያከናውን ተደረገ፣ በ1986 ዓ.ም በተደረገ የመዋቅር ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት የሚል ስያሜ ይዞ እንድሠራ ተደረገ፡፡
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 179/91 በሀገሪቱ የሚገኙ መዛግብትን መጻሕፍትንና መሠል ጽሁፎችን በአንድ ማዕከል ስር በማሰባሰብና በማደራጀት የሀገሪቱን የመረጃ አገልግሎት በተቀናጀ ሁኔታ መምራት የሚያስችለውን ህጋዊ ሰውነት አገኘ፡፡
  • በ1998 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው አዋጅ ቁጥር 471/98 የአስፈጻሚ መ/ቤቶች ስያሜ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት – ኤጀንሲ በሚል መጠሪያ እንዲለወጥ ተደርጎ የተጣለበትን ኃላፍነት በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Reply