እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መታሰቢያ ሀውልት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ-መቃብር ታንጾ ተመረቀ።

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በማስተዋወቅ የላቀ ሚና መጫወታቸውን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ገለጸ። የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ሚያዚያ 2፣ 2008ዓ.ም በተደረገው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ እንደገለፁት ሎሬቱ አገራዊ እሴትንና ስሜትን በማጉላትና በማጽናት ረገድ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

AAAA LORET

ሰዓሊው በጥበብ መስክ የአገሪቱን በጎ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ የተወጡት ድርሻ የተለየ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነም አንስተዋል። “ከገንዘብ በላይ የሆነ ቅርስን ትተው አልፈዋል” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ “የተለያዩ የፍልስፍና እና የነገረ ዕውቀት ማስተላለፊያ እንደሆኑ የሚታመንባቸውን የሥዕል ሥራዎቻቸውን በማሰባሰብ ለሕዝብ አውርሰው ማለፋቸውንም ገልጸዋል። የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ “ቪላ አልፋ” የተሰኘው የግል ሙዚዬማቸው በቅርስነት ለሕዝብ እንዲተላለፍ ማውረሳቸውን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ የዕውቀትና የጥበብ ክምችት የሆነው ቅርሳቸውን መንግሥት በልዩ ትኩረት ተረክቦ በሙዚዬም ደረጃ እንዲጠበቅ ኃላፊነቱ መውሰዱን ተናግረዋል።

     አንጋፋ ሰዓሊ ወርቁ ማሞ ለሎሬቱ መታሰቢያ መሰራቱና ለአገር ያበረከቱት የጥበብ ኃብት እውቅና እንዲሰጠው መደረጉን አወድሷል። የሎሬቱ አርአያነት ለአገርና ለትውልድም ጠቃሚነቱ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል። የንድፍ ሥራውን ያከናወነው ሰዓሊና ቀራጺ ግርማ ወልደሰማያት በሰጠው አስተያየት “ሎሬቱን አላወቅናቸውም፤ አልመረመርናቸውም” ሲል በቀጣይ ሥራቸው እንዲዳሰስ ጠይቋል፡፡
ምንጭ ፡- ኢዜአ

Leave a Reply