የዓለም የቦክስ ሻምፒዮኑ መሀመድ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

የዓለም የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻምፒዮኑ መሀመድ አሊ በ74 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ መሀመድ አሊ በመተንፈሻ አካል ችግር ባሳለፍነው ሀሙስ ሆስፒታል በመግባት ህክምናውን በመከታተል ላይ እያለ ህይወቱ ማለፉም ተነግሯል። የቀብር ስነ ስርዓቱም የትውልድ ስፍራው በሆነችው ኬንታኪ ሉሲቫይል እንደሚካሄድ መሀመድ አሊ ቤተሰቦች ቃል አቀባይ አስታውቋል። በህይወት ዘመኑ በርካታ ክብር ሽልማቶችን የተቀዳጀው መሀመድ አሊ፥ እንደ እወሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1999 የክፍለ ዘመኑ የምንግዜም ስፖርተኛ ተብሎም ተሸልሟል።
13325676_1784358761793125_6617126931369327869_n

መሀመድ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1960 በሮም ኦሎምፒክ ላይ በቀላል ሚዛን በመሳተፍ ነበር ያገኘው። በዚያው ዓመት ወደ ፕሮፌሽናል ቦክሰኝነት የተዘዋወረው መሀመድ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1964 እስከ 1967፣ ከ1974 እስከ 1978 እንዲሁም ከ1978 እስከ 1979 ድረስ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ሊሆን ችሏል። 61 ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድሮችን ያካሄደው መሃመድ አሊ ከነዚህ ውስጥ 37 ጨዋታዎችን በዝረራ እንዲሁም 19 በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈ ሲሆን፥ በ5 ጨዋታዎች ብቻ ነው የተሸነፈው።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Reply