የአፍሪካ የመጀመሪያው ኤር ባስ አውሮፕላን ”ሰሜን ተራሮች” ተብሎ ተሰየመ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ የመጀመሪያው የሚያደርገውን ኤር ባስ አውሮፕላን ”የሰሜን ተራሮች” በማለት ሰየመ። አየር መንገዱ በቅርቡ የሚረከበውን ኤር ባስ 350 ኤክስ ደብሊው ቢ(XWB) አውሮፕላን በአገሪቷ ዋነኛ የቱሪስት መስህብ በሆነው አካባቢ ስም ሰይሞታል። ለአፍሪካና ለኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሚሆነው አውሮፕላን ለመንገደኞች የተሻለ ምቾት የሚሰጥና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ መሆኑ ተመልከቷል።

511045bd606e73600ff9101ede9e0a41_XL

አየር መንገዱ ለኤር ባስ አውሮፕላኖች ቅድመ ክፍያ የሚሆነውን ከ107 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አይ ኤን ጂ ከተባለ ኩባንያ ማግኘቱን ባለፈው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል። ከኤር ባስ ኩባንያ 14 አውሮፕላኖች ማዘዙም ይታወቃል። ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም እንደገለጹት፤ ከአየር መንገዱ ራዕይ አንዱ የኤር ባስ አውሮፕላኖች ማግኘት ነው። አየር መንገዱ እስካሁን የሚጠቀምባቸው የቦይንግ አውሮፕላኖችን መሆኑ ይታወቃል። በአፍሪካ የአቪዬሽን ኢንዱሰትሪ ቀዳሚ የሆነው አየር መንገዱ የተመሰረተበትን 70 ዓመታት አገልግሎቱ በማክበር ላይ ነው።

                                                                                                                                                                        ምንጭ :- ኢዜአ

Leave a Reply