“ዘማቹ ጓዴ”……………..

በ197ዐ ዓ.ም መጨረሻ ላይ በአምባሣደር ቲያትር ቤት ተቀጥሮ ፤ መድረክ ላይ የተጫወተው “ማንበብ እና መፃፍ” የሚል ስራውን ነበር፡፡ ብዙዎች ይህንን የፀሃዬ ዮሀንስ የመጀመሪያ ስራ አድርገው ይቆጥሩታል ይሁንና እሱ ግን ከዚህ በፊት ብርሃን ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት እያለ የእድገት በህብረት መዝሙሮችን ይጫወት ነበር፡፡ ለአብነትም “ዘማቹ ጓዴ” የተሠኘውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ “ማንበብ እና መፃፍ” የተሠኘው ዘፈን ግጥም ደራሲ ዳምጠው ሲሆን ዜማው የራሱ የፀሃዬ ዮሀንስ ነው ፡፡ የሀሣቡ መነሻ ደግሞ በጊዜው በአምባሣደር ትያትር ቤት በርከት ያሉ ያልተማሩ ሰዎች መኖር ነበር፡፡ ዘፈኑ ከመሠተረ ትምሀርት አዋጁ ቀደም ብሎ የተሠራ ቢሆንም ከአዋጁ በኋላ ግን ድምፃዊ ፀሃዬ ከፍተኛ ታዋቂነትን አግኝቶበታል፡፡
13962605_1397450693603609_6571705851272105002_n

ከአምባሣደር ትያትር ቤት ወደ ራስ ቲያትርም ተዛውሮ ከ1973 -1983 ዓ.ም ድረስ ያገለገለው ፀሃዬ ዮሀንስ በዚህ ቆይታው በርከት ያሉ ዘፈኖችን በካሴት አሣትሞ ለህዝብ አድርሷል፡፡ የመጀመሪያ ካሴቱ “ተይ ሙኒት” ሲሆን ፍንጭቷ፣ ብቸኝነቴን፣ ማን እንደ ሀገር፣ ያላንቺማ ፣ እረ ስንቱን ፣ ተባለ እንዴ ፣ ለትንሽ እና ሳቂልኝ እያለ ቀጥሎ በቅርቡም “የኔታ” የተሠኘ አልበሙን ጀባ ብሎናል፡፡
13882567_1397450696936942_5198654870878210213_n

በ1975 ዓ.ም አካባቢ “ፍንጭቷ” የተሠኘውን ስራውን በካሴት ሲያሣትም ብዙዎቹ የዘፈን ግጥም ድርሰቶች የጋዜጠኛ ልዑል አማራ ነበሩ፡፡ በተለይ “ፍንጭቷ” የተሰኘው ዘፈን ደራሲው የፃፈው “ፍንጭቱ” በማለት ራሱን ፀሃዬ ዮሀንስ መነሻ በማድረግ ነበር የሰራው፡፡ ፀሃዬ ግን “ፍንጭቱ” የሚለው ወደ “ፍንጭቷ” በመቀየር ተጫውቶታል ፡፡ ይህን ዘፈን በጣም እንደሚወደው ፀሃዬ ዮሀንስ በአንድ ወቅት ገልፆ ነበር፡፡ ለጎዳና ተዳዳሪዎች “የጥቁር አበቦች” የሚል ስራ የተጫወተው ፀሃዬ ዮሀንስ እናቱን በሞት እንዳጣም ለእናቱ “ምትክ አልባ እናቴ” የተሰኘ ስራ ተጫውቷል፡፡ ለድምፃዊ ፀሀዬ ዮሀንስ እድሜ እና ጤና በመመኘት ቀሪውን እናንተ ጨምሩበት…….

Leave a Reply