ኑ ግድግዳ እናፍርስ……

“አንዱ በአንዱ ላይ እየተጨካከነ ነው፤ ነጋዴው ለተጠቃሚው አይራራም፡፡ በየሙያው እና በየዘርፉም ሰበአዊነት የጎደላቸው ጥቂት የሚባሉ አይደለም፡፡ ትርፍ ማጋበስ ሌሎችን አጥንታቸውን እያስገጠጠው ነው፡፡ እየፈረሱ ያሉ ልቦች አሉ፤ ልቦችን እያፈረሱ ያሉ ሰዎችም አሉ፡፡ በዚህም ኑሮ መከራ የሆነባቸውን ቤት ይቁጠራቸው ……

15578413_1542947882387222_6656775409737482421_n

የ1ብር እቃ 10 ብር የሚሸጥ ከሆነ ይሄ ሰው ከማጅራት መቺ በምን ይለያል፤ ጀሶ ደባልቀው በሚሸጡት እንጀራ ሰው እየሞተ አይደለም ወይ? ህይወት የሚባለው ነገር ጣራው እየተገነጠለ ፣ ግድግዳው እየፈረሰ አይደለም ወይ? የሚፈርስ ጣራ እና ግድግዳ ብቻ ሳይሆን ልቦናም ጭምር ነው፡፡ ኑ ግድግዳ እናፍርስ ከጣራ እና ግድግዳም በላይ ነው፡፡ የአንዱ ግድግዳ ሲፈርስ የራስ ገበና ይገለጣልና ሁሉም በየዘርፉ እና በየሙያው ይታይ …” ስለዚህ ለሀገር እና ለወገን ቀና ቀናውን ፣ መልካም መልካሙን እናስብ…..!!!

Leave a Reply