እርስዎ ያረጁ አይመስልም ለምን ? “የባህል ነጭ አልባሳቴን ስለምለብስ ነዋ….”

አጠር ደልደል ያሉ መልከ መልካም እና ቀናኢ ሰው ናቸው፡፡ የፀጉራቸው ሽበት የእድሜ ባለፀጋነታቸውን ያሳብቃል፡፡ መልካቸውን እና ሰውነታቸውን ተመልክቶ እድሜያቸውን ለሚገምት ሰው የሚቀራረብ ነገር ለመጥራት ይቸገራል፡፡ ከዚህ በመነሳትም ብዙዎች ምነው እርስዎ አያረጁም ገና ወጣት ነው የሚመስሉት ብለው ይጠይቋቸዋል፤ የእሳቸው ምልስም “የባህል ነጭ አልባሳቴን ስለምለብስ ነዋ” የሚል ነው፡፡

እውን የባህል አላባሳት /ነጫጭ ልብሶች/ አያስረጁም …. ? ልባቸው ደንዳና ወኔያቸው ብርቱ በመሆኑ አሁንም ለእርጅና እጅ አልሰጡም ፡፡ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ “አናረጅም እኛ” ብላ ያቀነቀነችው በእኔ እሳቤ ለእሳቸው ሁነኛ ዜማ ነው፡፡ እኚህ ሰው እድሜያቸው ስንት ሆኖ ነው ማለታችሁ ስለማይቀር እሱን ላስቀድም 94 አመታቸው ነው፡፡ እኔ የባህል ተቆርቋሪ እና አምባሳደር ብያቸዋለሁ ፡፡

እማማ ፅዮን አምዶም የመጀመሪያዋ የሴቶች የባህል ፋሽን ዲዛይነር ናቸው፣  የባህል ልብሶችን በዘመናዊ መንገድ በመስራት ይታወቃሉ፡፡ አንዳንዶች የመጀመሪያዋ ሴት ነጋዴም ይሏቸዋል፡፡በ1960ዎቹም “ፅዮን ጥበብ” የተባለ የራሳቸው የፋሽን መፅሄት አዘጋጆች ቀጥረው ያሳትሙ ነበር ፡፡ “ፅዮን ጥበብ” የተሰኘ ሱቅም መስቀል አደባባይ አካባቢ ከፍተው ሰርተዋል፡፡ ወዲህ ደግሞ የጄኔራል አማን አምዶም እህት….. እድሜ እና ጤና ተመኘሁ ፣ በተረፈ እናንተ ጨምሩበት …..

Leave a Reply