አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በ2 ሺህ ሜትር ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች፡፡

የሶስት ጊዜ የቤት ውስጥ ሻምፒዮንና  የ1500 ሜትር ክብረ  ወሰን ባለቤት  የሆነችው አትሌት ገንዘቤ  ዲባባ የአውሮፓዊያኑ  2017 የውድድር ዘመኗን በአዲስ ክብረ  ወሰን እና ድል ጀምራለች። ትላንት በስፔን ሳባዴል በተካሄደው የቤት ውስጥ ውድድር እ.ኤ.አ በ1998  በገብሬልሻ ሳዛቦ ተይዞ የነበረውን ምርጥ ሰዓት ገንዘቤ  በሰባት ሰከንድ በማሻሻል 5:23.75 በሆነ ጊዜ ማሸነፍ ችላለች።

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ1998 በሮማኒያዊቷ አትሌት ጋብሪዬላ ዛቦ ተይዞ የነበረውን የ2 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ክብረወሰን በ7 ሰከንድ በማሻሻል የግሏ ማድረግ ችላለች። በዚህም አትሌት ገንዘቤ ትላንት በስፔን ያስመዘገበችው ድል በቤት ውስጥ ሻምፒዮና ያስመዘገበችውን ድል ወደ ስድስት ያሳድገዋል። አትሌቷ ከዚህ በፊት በአንድ ማይል፣ በሁለት ማይል፣ በ1500ሜትር፣ በ3000ሜትር፣ በ5000ሜትር ጭምር የአለም ፈጣን ሰዓት ክብረ ወሰን ባለቤትም ነች።

Leave a Reply