እንዲህ ናት ሀገሬ!!!

ሰለሞን ባረጋ እና ዘይነባ ይመር የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አሸንፈዋል፡፡ ታላቁ ሩጫ በዘንድሮው ውድድር ላይ ክብረወሰን የሆነ 44 ሺህ ተሳታፊዎች የነበሩት ሲሆን፥ ከ26 የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ የውጪ ሀገር ተሳታፊዎች ተካፍለዋል። ውድድርም በኢትዮጵያውኑ አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቋል።

በ10 ኪሎ ሜትር ወንዶች
1ኛ.ሰለሞን ባረጋ
2ኛ.ሞገስ ጥዑማይ
3ኛ.ዳዊት ፍቃዱ

በሴቶች ደግሞ
1ኛ.ዘይነባ ይመር
2ኛ.ግርማዊት ገብረእግዚሃብሄር
3ኛ.ፎተን ተስፋዬ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

 

ለየምድቡ አሸናፊዎች 100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በውድድሩ ላሸነፉ አትሌቶች በጠቅላላው 300 ሺህ ብር መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ ሲ ኤን ኤን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሚድያዎች ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ሽፋን ሰጥተዋል፡፡ ከውድድሩ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ለዕርዳታ እንደሚዉል የታላቁ ሩጫ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ ዜና ዛሬ በተካሄደው 17ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስተውቋል። ለሞቱት ወገኖቻችን ነፍስ ይማር እያልን ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡
ፎቶ ፡- ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ